አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መብረዱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል ተከስቶ የነበረው ግጭት መብረዱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ
አርትስ 12/03/2011
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት ዲሳሳ እንደተናገሩት ተፈጥሮ የነበረው ሁከት በመብረዱ ተማሪዎችን ጭምር በማወያየት ችግር ፈጣሪዎቹን ለመለየት እየተሰራነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሐይማኖት እንደገለፁት በትላንትናው ዕለት በሁለት ተማሪዎች መካከል የተከሰተ ግጭት ሰፍቶ በአጠቃላይ 34 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ከተጎጂዎቹ ውስጥ የ 29ኙ ቀላል ጉዳት በመሆኑ ወዲያው ህክምና ተደርጎላቸው ተመልሰዋል፡፡5 ያህሉ ደግሞ በአሶሳ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስም በስፍራው ተገኝተው ግጭቱን እንዳረጋጉት ተሰምቷል፡፡