ግብፅ እንኳን ለራሴ ለዓረብ ጎረቤቶቼ እተርፋለሁ እያለች ነው
ግብፅ እንኳን ለራሴ ለዓረብ ጎረቤቶቼ እተርፋለሁ እያለች ነው
አርትስ 28/02/2011
የግብፁ ፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ የአረብ ባህረ ሰላጤ ሀገራት ከየትኛውም ወገን ቀጥተኛ የአደጋ ስጋት የሚቃጣባቸው ከሆነ ከሆነ ሀገሬ ሀይሏን ለማንቀሳቀስና ፀብ አጫሪዎችን ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡
አልሲሲ ይህን ያሉት የመዝናኛ ከተማ በሆነችው ሻርም አል ሼክ በወጣቶች ፎረም ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ፕዝዳንቱ በአረብኛ ለሚተላለፈው ስካይ ኒውስ ሲናገሩ የዓረብ ሀገራት ብሄራዊ ፀጥታ አደጋ ላይ እንዲወድቅ አንፈቅድም ነው ያሉት፡፡
አልሲሲ በተለይ ኢራንን በስም ጠቅሰው በሌሎች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ተስፋ እናደርጋለን በማለት በሻርም አል ሼኩ ኮንፈረንስ ላይ የአደጋ ስጋቱ ከየት አቅጣጫ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚካሄደው ትልቅ ለውጥ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነትም አስታያታቸውን ሰጥተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በኢትዮጵያ ለውጡን ከሚያራምደው አዲሱ አመራር ጋር መልካም ውይይቶቸችን ለማድረግ እንፈልጋለን ያሉት አልሲሲ ዋና ዋናዎቹን የአፍሪካ ችግሮች ግን የአፍሪካ ህብረት ይፈታቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ጉዳይ ጣልቃ እንደማትገባ ተስፋ እናደርጋለን በማለት በሻርም አል ሼኩ ኮንፈረንስ ላይ የአደጋ ስጋቱ ከየት አቅጣጫ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚካሄደው ትልቅ ለውጥ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ስላለው ግንኙነትም አስታያታቸውን ሰጥተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
በኢትዮጵያ ለውጡን ከሚያራምደው አዲሱ አመራር ጋር መልካም ውይይቶቸችን ለማድረግ እንፈልጋለን ያሉት አልሲሲ ዋና ዋናዎቹን የአፍሪካ ችግሮች ግን የአፍሪካ ህብረት ይፈታቸዋል የሚል እምነት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡