Uncategorized

ለኦባማ እና ለሂላሪ በአድራሻቸው የተላከ ተቀጣጣይ ቁስ ተያዘ

አርትስ 15/02/2011

 

ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ እና ለቀድሞዋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን የተላኩ ሁለት የታሸጉ ተቀጣጣይ ቁሶች በፖሊስ መያዛቸውን የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

ለሂላሪ የተላከው ተቀጣጣይ ቁስ ማክሰኞ ዕለት በኒውዮርክ ከመድረሱ በፊት የተያዘ ሲሆን ለኦባማ የተላው ፈንጂ ደግሞ ትናንት ዋሽንግተን በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተቀጣጣይ ቁሶቹ በአግባቡ የታሸጉ እንደነበሩና በፍተሻ ወቅት  እንደተያዙ ታውቋል፤ በዚህም ጉዳት እንዲደርስባቸው ታስቦ መልዕክቱየተላከላቸው የቀድሞ ባለስልጣናት ለአደጋ ከመጋለጥ ተርፈዋል ፡፡

የደኅንነት መስሪያ ቤቱ የመልዕክቶቹን ምንጮች እየመረመረ መሆኑን እና ተቀጣጣይ ቁሱ   ከሁለት ቀናት በፊት በቢሊየነሩ ጆርጅ ሶሮ ቤትከተላከው ፈንጂ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት አስታውቋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ሁኔታው ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀሙት ሰዎች ለህግ እስከሚቀርቡ ድረስ  ማናቸውንም የፖስታ መልዕክቶች ወደሁለቱሰዎች ከመድረሳቸው በፊት  አስጊ አለመሆናቸውን የደህንነት መስሪያቤቱ  ይመረምራል ብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button