EthiopiaPolitics

አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን በወይት ሀውስ አቀረቡ፡፡

አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውንዋይትሀውስ አቀረቡ፡፡

በአሜሪካ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ፍፁም አረጋ የሹመት ደብዳቤያቸውን በኋይት ሀውስ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ነው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት፡፡

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በወቅቱ እንደተናገሩት፥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት እያደረገ ያለው ለውጥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የመሪነት ሚና በአግባቡ እየተወጣች መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚሰሩ በመግለፅ፤ ለአምባሳደር ፍፁም የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አስተላልፈዋል።

አምባሳደር ፍፁም አረጋ በበኩላቸው፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ወዳጅነት ለማስቀጠል እንደሚሰሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።

በተለይም በኢኮኖሚ እና በቀጣናዊ ሰላም ዙሪያ በማተኮር ኢትዮጵያና አሜሪካ በጋራ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት ይበልጥ ለማዳበር  አበክረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button