Africa

የህዳሴ ግድቡ ሃይል ማመንጨት መጀመርና የግብጽ ቅሬታ…


አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2014 ኢትዮጵያበግድቡ ዙሪያ የተናጠል ውሳኔ በማሳለፍ መርህ የመጣስ ተግባሯን ቀጥላበታለች ስትል ግብጽ ቅሬታዋን አሰማች፡፡የግብፅ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የህዳሴ ግድቡን የመጀመሪያው ሃይል የማመንጨት ስራ ይፋ መሆን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን እርምጃ መርህን የሚጻረር ብሎታል፡፡ ከአሁን ቀደም የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ሲከናወን ተመሳሳይ ተቃውሞ ያሰማችው ግብፅ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ2015 የፈረመችውን ስምምነት መጣሷ ስህተት መሆኑን በመጥቀስ ድርጊቱ ግብፅን የሚጎዳ ነው ብላለች፡፡

ካይሮ በዚያን ወቅት የተፈረመው ስምምነት የታችኞቹ ሀገራት ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የሚከላከል ነው ስትል ኢትዮጵያ በበኩሏ ግድቡ የተፋሰሱን ሀገራት የሚጎዳ እንዳልሆነ በተደጋሚ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ የመጀመሪያው የሃይል ማመንጨት ስራ በይፋ ሲመረቅ በስፍራው የተገኙት ጠቅላይ ሚ ኒስትር ዐቢይ አህመድ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ጎረቤቶቿን የመጉዳት ዓላማ እንደሌላት ገልጸው በአባይ ወንዝ ከመጠቀም ግን ማንም አያቆማትም ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ተከታታይ ውይቶችን ቢያደርጉም የሁለቱ ሀገራት አቋም ከኢትዮጵያ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳቃታቸው የግድቡ ግንባታ ቀጥሎ እዚህ መድረሱን ኢጂፕት ቱዴይ ዘግቧል፡፡ 78 ቢሊዮን ኪዊቢክ ሜትር ውኃ የመያዝ አቅም ያለው የህዳሴው ግድብ በሁለት ዙሮች ሙሌት 8 ቢሊዮን ኪዊቢክ ሜትር ውኃ መያዙን ዘገባው አክሎ ገልጿል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button