EthiopiaSocial

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የባህል ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የባህል ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል

ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው የኢትዮጵያ እና ኤርትራን የህዝብ ለህዝብ ትስስር  ለማጠናከር መሆኑን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ቡድኑ እውቁ  ኤርትራዊ አርቲስት በረከት መንግስተአብን ጨምሮ 55 አባላት ያሉት ነው ተብሏል፡፡

የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድኑ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጋር በመሆን የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎችን ያቀርባል፡፡

የፊታችን የካቲት 9 ቀን ባህርዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ፣ የካቲት 12 በሀዋሳ እና የካቲት 14 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተሞች በሚካሄዱ ባህላዊ የሙዚቃ ዝግጅቶችን የሚያቀርቡ ሲሆን ፤

በሚቀጥለው ወር ደግሞ የሁለቱን ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ እና የባህል ቡድን ወደ ኤርትራ የሚያቀና መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል ።

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button