Uncategorized

አንካራና ዋሽንግተን ብድር በመመላለስ የንግድ ጦርነቱን አጧጡፈውታል፡፡

ቱርክ በአሜሪካ ምርቶች ላይ እስከ 140 በመቶ የሚሆን ታሪፍ ጣለች፡፡ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን አሜሪካ በሀገሬ ላይ ያወጀቸው ኢኮኖሚያዊ ጥቃት መልስ ያስፈልገዋል ሲሉም ተደምጠዋል፡
ኤርዶሀን ባለፈው ሰኞ በሰጡት መግለጫ ከእንግዲህ ከአሜሪካ የሚገቡ የኤሌክትኒክስ ምርቶች በቱርክ ገበያ ቦታ የላቸውም ብለው ነበር፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው የቱርክ መንግስት በአሜሪካ ምርቶች ላይ ሌላ ተጨማሪ ታሪፍ ጥሏል፡
በዚህም መሰረት የሲጋራ ምርቶች ላይ 60 በመቶ፣ ተሽከርካሪዎች ላይ 120 በመቶና በአልኮል መጠጦች ላይ የ140 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል የሚያዘው ሰነድ ላይ ፕሬዝዳንት ኤርዶሀን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በሁለቱ ሀገሮች መካከል ያለው ውጥረት ከፍ ብሏል ነው የተባለው፡፡
ዶናልድ ትራምፕ አንካራ ያሰረቻቸውን ፓስተር እንድትፈታ ላቀረቡት ጥያቄ የእምቢታ መልስ አጸፋ ተጨማሪ ታሪፍ በመጣላቸው ነው ቱርክ ይህን ውሳኔ ያሳለፈችው ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button