Social

ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የአሻራ ምርመራ አገልግሎት ተጀመረ

ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የአሻራ ምርመራ አገልግሎት ተጀመረ።

ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ የፎረንሲክ ምርመራ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ አገልግሎቱን  ሚያዚያ 14/2011 ጀምሮ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱ ወደ መካከለኛው ምስራቅ አገራት ተቋርጦ የነበረው የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዞ በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የጋራ ስምምነት ለመጀመር ያስቻለ መሆኑን የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት አመልክቷል፡፡

ወደ መካከለኛው ምስራቅ የስራ ስምሪት ስምምነት ወደተደረገባቸው 3 አገራት ማለትም ሳውዲ አረቢያ፤ዮርዳኖስና ኳታር የሚሄዱ ተገልጋዮችን ተቀብለው እያስተናገዱ መሆናቸውን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ቢሮ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት የአሻራ ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊው ኮማንደር ተፈሪ አርጋው ለኢቢሲ ገልፀዋል፡፡

ተገልጋዮች ወደ አሻራ ምርመራ ሲመጡ የታደሰ ፓስፖርት፤የህጋዊ ኤጀንሲ ደብዳቤ፤ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ እና አስር የኢትዮጵያ ብር በመያዝ በስራ ሰዓት መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን  ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button