EthiopiaSocial

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ወደ አዳማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች የሚገቡ ተማሪዎችን ለ3ኛ ጊዜ (online)ፈትኜ ላስገባ ነው አለ፡፡

በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ስር የሚገኙት የአዳማ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች ለ2011 የትምህርት ዘመን የመሰናዶ ትምህርት ጨርሰው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትና ለፈተና ከቀረቡት 4700 ተማሪዎችን በማወዳደር 3000 ተማሪዎች እንደሚቀበል ተናግሯል፡፡
ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገፁ እንዳሰፈረው ፈተናው ነገ ረቡ በ30/12/2010 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እስከ 11፡00 በተለያዩ ክልሎች ባሉ 37 ዩኒቨርስቲዎች በቀጥታ( online) የሚሰጥ ሲሆን የመግቢያ ውጤቱ ለታዳጊ ክልሎች፣ ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች ዝቅ እንዲል ይደረጋል ፡፡
ተፈታኞች ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ሂሳብ እና ኢንግሊዝኛ ፈተና የሚወስዱ ሲሆን ዝቅተኛው የማለፊያ ውጤት ከ50 በላይ ሆኗል፡፡
ይህ በየቀጥታ( online) ፈተና እንደሀገር በሀገር አቀፍም ሆነ በክልል ደረጃ የሚሰጡ ፈተናዎች ከአንድ ማእከል በማስተላለፍ ኩረጃን፣ የወረቀት ብክነትን እና የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ
እንደሚያደርግ ነው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በገፁ የገለጸዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button