EthiopiaPolitics

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በመሆን በዛሬው እለት ተሹመዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በንቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በመሆን በዛሬው እለት ተሹመዋል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል ስላልሆኑ ነው የተባለ ሲሆን፥ በምክር ቤቱ ደንብ መሰረት የምክር ቤቱ አባል ያልሆነ ሰው ከንቲባ መሆን አይችልም።

በምክትል ከንቲባነት የተሾሙት ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ስራን የሚሰሩ ይሆናልተብሏል።

ኢንጂነር ታከለ ከዚህ ቀደም የሱሉልታ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊ፣ እንዲሁም የሆለታ ከተማ ከንቲባ ሆነው አገልግለዋል፡፡

እንዲሁም ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው በማዕረግ ተሹመዋል።

ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ የነበሩ ሲሆን ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የአዲስ አበባ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button