EthiopiaSport

በመጭው ዓርብ ሊከናወኑ የነበሩ ተስተካካይ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ለሌላ ጊዜ ተላለፉ

አርትስ ስፖርት 27/02/2011
የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ሶስት ጨዋታዎች ከፀጥታ ጋር ስጋት በመኖሩና በብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ምክንያት ነው ለሌላ ጊዜ የተላለፉት። ፌዴሬሽኑ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ከተወሰነባቸው መካከል በባህር ዳር ከነማ እና ስሑል ሽረ መካከል ሊደረግ የነበረውን ጨዋታ ሲሆን ጨዋታው ለሌላ ጊዜ የተላለፈው ደግሞ የትግራዩ ቡድን ሽረ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ ወደ ሌላ ጊዜ እንዲዘዋወር ጥያቄ በማቅረቡ ነው፤ ባለሜዳው ባህር ዳር ከነማ ግን ጨዋታው በሰላም እንዲከናወን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን ቢገልፅም ፌዴሬሽኑ እንዲራዘም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ሌሎቹ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፉ የተወሰኑ ግጥሚያዎች ደግሞ ድሬዳዋ ከነማ ከ ደቡብ ፖሊስ ሐረር ላይ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ሲሆን ድሬዳዋ ለዋልያዎቹ እና ለ23 ዓመት በታች ቡድን አምስት ተጫዋቾች በማስመረጡ ምክንያት በተመሳሳይ ሲዳማ ቡና አራት ተጫዋቾች በማስመረጡ፤ የወላይታ ድቻ እና የሲዳማ ቡና ጨዋታም ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉቸው ታውቋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button