EthiopiaPoliticsSocialUncategorized

የፀረ ሽብር እና የበጎ አድራጎት ማህበራት ድርጅት አዋጅ ህዝብ ሊወያይበት ነዉ፡፡

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፍትህ ጉዳዮች የኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታዬ ደንዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ የበጎ አድራጎት ማህበራት ድርጅቶች አዋጅ እና የፀረ ሽብር ህጉን ለማሻሻል ከሁለት ወር በፊት ኮሚቴ መቋቋሙን አስታውሰው፤ ኮሜቴው በተለያዩ ዘርፎች ውሰጥ የፍትህ ስርዓቱን ክፍተት በመመርመር ለቀጣይ ሦስት አመት የሚሆኑ እስትራቴጂክ ዕቅድ አስቀምጧል፡፡
የሌሎች ሀገራትን ልምድ በመውሰድ ከቁጥጥር ይልቅ ነፃነትን ፤ከገዳቢነት ይልቅ ፍቃድን በተለይም ድርጅቶች እና ማህበራት ፍቃድ የሚያገኙበትን ዴሞክራሲ የተሞላበት እንቅስቃሴ የሚያደርጉበበትን አሰራር በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ህጉ ከመውጣቱ በፊትም የሚሻሻልበት መድረክ ለመፍጠር ከነሃሴ 25 እስከ መስከረም 10 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በዘጠኝ ክልሎች እና ከተሞች የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፤ ምሁራን እና የሚዲያ በለሞያዎች ያሣተፈ ህዝባዊ ምክክር እንደሚደረግ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

አርትስ 23/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button