Uncategorized

ሪያድ የሀጂ ጉዞን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይቻልም አለች፡፡

ሪያድ የሀጂ ጉዞን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይቻልም አለች፡፡
የሳውዲ አረቢያ የኢንፎርሜሽን ሚንስትር አዋድ ቢን ሳልህ አልዋድ እንዳሉት ወደ ቦታው የሚጓዙ ምእመናን ከጉዞው ሀይማኖታዊ በረከት እንጂ የፖለቲካ ትርፍ ፍለጋ እንዳይደክሙ አሳስበዋል፡፡
ሚንስትሩ ይህን ያሉት ጅዳ ውስጥ ከአረብ ከአፍሪካና ከእስያ ሀገራ የተወከሉ ልኡካን ጋር ተገናኝተው በጉዞው ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ነው፡፡
አልዋድ እንዳሉት ሀገራቸው ከየትኛውም የዓለም ክፍል ወደ ሀገራቸው ለሚገቡ የእምነት ተጓዦች ስነስርዓቱን ፈጽመው እስኪመለሱ አስፈላጊውን መስተንግዶ ለማድረግ ዝግጁ ናት፡፡
ነገር ግን ይህ የማምለኪያ ቦታ እንጂ የፖለቲካ መድረክ አይደለም ያሉት ሚንስትሩ ማንም ሰው ይህን መገንዘብ አለበት ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አልዋድ ይህን ያሉት ኳታር ሳውዲ አረቢያ የሀጂ ጉዞ በሚያደርጉ ዜጎቼ ላይ ችግር እየፈጠረች ነው ብላ መክሰሷን ተከትሎ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button