EthiopiaSportSports

ለሁለት ቀናት በስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል ምንጮች ላይ የተካሄደው ውይይት ተጠናቀቀ

የስፖርታዊ ጨዋነት ምንጮች በሚል በቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የተዘጋጀው ፕሮግራም ባለፉት ሁለት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት ተጠናቅቋል፡፡

በውይይቱ የሁለት ቀናት ቆይታ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት በባለድርሻ አካላት መካከል ምክክር ተደርጓል፡፡

አጠቃላይ ውይይቱ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት በኩል በተሰጡ የማጠቃለያ ሀሳቦች የአቋም መግለጫ ተጠናቅቋል ፡፡

ከመንግስት በኩል አቶ ሀብታሙ ሲሳይ ‹‹መንግስት መግባት ያለበት ቦታ አለ ነገር ግን በትልቁም በትንሹም ገብተን አንፈተፍትም። ስለ ስፖርታችን ታሪካዊ አመጣጥ ሰነዶችን አገላብጠን ያየን አይመስለኝም፤ የትምህርት እና ስልጠናው ፍኖተ ካርታ ላይ እንዲካተት ስፖርቱን እያደረግን እንገኛለን›› ፡፡

የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን ‹‹መድረኩ አላማውን አሳክቷል፤ ሁላችንም የሚያስተሳስረን ኢትዮጵያዊነት አለ፤ ዛሬ ደስታ ተሰምቶኛል ›› ፡፡

ከፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው ‹‹ጉዳዮችን በደንብ አውጥቶ መወያየት ያስፈልጋል። ስፖርት ለሰላም ለፍቅር የሚለው ሳይሆን ለትግል የሚለው ነው ገኖ የወጣው ምንም አይነት አይነት ቴክኖሎጂ ቢያጅበን ስፖርት ለፍቅር ለአንድነት ለመቻቻል ካልሆነ አደጋ አለው። ሁሉን ነገር ትተን ስራችንን በፍቅር ብናስኬድ የተሻለ ነው ›› ፡፡

ከፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ ‹‹ሜኑ ቀርቦለት በፈለገበት ባህል እና ቋንቋ የተወለደ አለ ካላችሁ ንገሩኝ፤ ነገሮችን ከመግፋት ወደ እኛ መውሰድ አለብን፤ የተሳሳተን ዳኛ እንደ ነፍሰ ገዳይ ምናየው ለምን እንደሆነ አይገባኝም፤ ዳኛ ስንመድብ ዘር እየቆጠሩ ተቸግረናል፤ አንድን ክለብ ለመበደል አንዱን ለመጥቀም አይደለም፤ ክለቦች ጋር የተነሳው ችግር ሜዳዎቻችን ችግር ያሉባቸው ናቸው፤ ይህንን ለማረም እንሞክራለን›› ።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት ‹‹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ስፖርት መርህ እየተጓዘ ይገኛል፤ ጥሩ የሁለት ቀን ውይይት ተደርጓል። ይህ አይነት ውይይት ወደፊትም ይቀጥል። ለህግ እና ለመርህ ተገዢ ለመሆን እንስራ››፡፡

                                                                                                             መረጃው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button