SportSports

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ይከናወናሉ

 

የሊጉ የ35ኛ ሳምንት መርሀግብር ግጥሚያዎች ቅዳሜ ሲጀመሩ ስድስት ያህሉ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡

ለሊጉ ሻምፒዮንነት ቁልፍ ሚና ያለው  ጨዋታ ቀን 8፡30 ላይ ሲከናወን ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ ቶተንሃም ሆትስፐርን ያስተናግዳል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በተመሳሳይ ስታዲየም ከቀናት በፊት በቻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ተገናኝተው ሲቲ ማሸነፍ ቢችልም፤ ከውድድሩ ተሰናብቷል፡፡

ስፐርሶች በነገው ጨዋታ የሙሳ ሴሶኮን ግልጋሎት የማያገኙ ሲሆን ኢሪክ ዳዬር ከወገብ ጉዳቱ ተመልሶ ልምምድ መስራት መጀመሩ ተነግሯል፡፡

ለአራትዮሽ ዋንጫ የሚያርጉት ግስጋሴ ከቻምፒዮንስ ሊጉ ስንብት በኋላ የተጨናገፈባቸው ውሃ ሰማያዊዎቹ ፤ ለፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ የሚያደርጉትን ትግል እንዳይስተጓጎልባቸው የነገው ጨዋታ ውጤት ወሳኝ ነው፡፡   

ስፐርሶችም ቢሆን በደረጃ ሰንጠራዡ ከአንድ እስከ አራት ያለው ደረጃ ውስጥ ለማጠናቀቅ ጥረት ላይ በመሆኑ በቀላሉ እጅ አይሰጡም፡፡

አመሻሽ 11:00 ላይ በተመሳሳይ ሰዓት አራት ፍልሚያዎች ሲደረጉ ቦርንመዝ ከ ፉልሃም ፣ ሀደርስፊልድ ከ ዋትፎርድ፣ ዌስት ሃም ዩናይትድ ከ ሌስተር ሲቲ እና ወልቨርሃምፕተን ከ ብራይተን ይጫወታሉ፡፡

ምሽት 2፡ 30 ደግሞ ኒውካስት ዩናይትድ ከሳውዛምፕተን ይፋለማሉ፡፡

በበነጋታው እሁድ ኤቨርተን 8፡30 ሲል ጉዱሰን ፓርክ ላይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ይጫወታሉ፡፡ ምሽት 1፡00 ላይ ደግሞ የሊጉ አናት ላይ የሚገኘው ሊቨርፑል ወደ ዌልስ ምድር አምርቶ የመውረድ ትልቅ ስጋት ያለበትን ካርዲፍ ሲቲ የሚገጥም ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት በለንደን ደርቢ አርሰናል ኤመሬትስ ላይ ከክሪስታል ፓላስ ይፋለማሉ፡፡

ሰኞ ደግሞ የሳምንቱ ማሳረጊያ ጨዋታ በቼልሲ እና በርንሊ መካከል ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ይደረጋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button