EthiopiaLegalRegions

በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ

በምዕራብ ኦሮሚያ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ

አርትስ 28/02/2011

የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው በትላንትናው  እለት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ  በሰጡት መግለጫ ፤የክልሉ መንግስት ህዝቡን መሰረት አድርጎ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ እየሰራያለው ስራ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በክልሉ በተወሰኑ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን እና በአፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ያለው የፀጥታ ሁኔታ መሻሻል ያለበት መሆኑን የክልሉ መንግስት ይገነዘባል ያሉት አቶ አድማሱ፥ በዚህ ላይም እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

 የክልሉ መንግስት የኦሮሞ ህዝብ ትጥቅ መፍታት አለበት የሚል አቋም እንደሌለው እና ማንኛውንም አካል በመማረክ የማስተዳደር ፍላጎት እንደሌለውም ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የክልሉ መንግስት በኦሮሞ ስም ተደራጅተው ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመወያየት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አድማሱ፤ ወደ ፊትም ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ በጠብመንጃ ሳይሆን በውይይት፣ በመደማመጥና በመከባበር የሚፈታ መሆኑን በመግለጽ፥ የክልሉ መንግስትም የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ በመመለስ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚወያይ መሆኑንም አስታውቀዋል።

አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች አሁን እየመጣ ያለውን ለውጥ ጠብቀው በማስቀጠል የበኩላቸውን እንዲወጡም አቶ አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button