COVID-19World News

ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 ኢራቅ 13 ዶክተሮቿ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ማጣቷን ይፋ አደረገች:: የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ካለፈው ፌብሯሪ ወር ጀምሮ ባለው ጊዜ ውስጥ 13 ዶክተሮቿ በኮቪድ 19 ሞተውባቸዋል፡፡ የኢራቅ የሀኪሞች ማህበር ሀላፊ አብዱል አላሚር አል ሺማሪ በመላ ሀገሪቱ ከ700 በላይ ዶክተሮች በበሽታው መያዛቸውን ተናግረዋል፡፡ ሀኪሞቻችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለመርዳት የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው ያሉት ሀላፊው ይህን በሚያደረጉበት ወቅምት ራሳቸውን ሰውተዋል ብለዋል፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው የኢራቅ የጤና አጠባበቅ ስርዓት ደካማ በመሆኑ ሀገሪቱ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ከባድ ችግር ውስጥ ገብታለች፡፡ ኢራቅ በአሁኑ ወቅት ከ45 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙባት ሲሆን ከ1 ሺህ 700 በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሰቢያ ህይዎታቸው አልፏል፡፡ መንግስት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ከፊል የሰዓት እላፊ ገደብ፣ በርከት ያሉ ሰዎች እንዳይሰባሰቡና የፊት መሸፈኛ ጭብሎችን እንዲያደርጉ በህግ ደንግጓል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button