EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ከሄድን ለኢትዮጵያ እንደፌደራሊዝም ጠቃሚ ስርዓት የለም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ

የብሄር ማንነትና የኢትጵያዊ ማንንት እስከዛሬ በሚዛናዊነት መሄድ አልቻሉም እነዚህን ማንነቶች እንደሚተባበሩ ሳይሆን እንደሚተካኩ ማንነቶች መታየት የለባቸዉም በቀጣይም የሁለቱን ማንነቶች ሚዛን አስይዘን ለማስቀጠል ርብርብ እናደርጋልን ብለዋል በንግግራቸዉ፡፡
ዜጎች መታወቂያ የማያገኙበት በገዛ ገንዘባቸዉ የሚፈልጉትን የማይሸምቱበትን ስርዓት የመልካም አስተዳደር ችግር ብለን ከምናሽሞነሙን የመጥፎ አስተዳደር መስፍን ብለን ልንታገለዉ ይገባል ብለዋል
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸዉ ጉባኤዉ የሀገሪቷን ቀጣይ ጉዞ የሚወሰንብትነዉ ያሉ ሲሆን ፡ሀገር የምትድነዉ በቅብብሎሽ ነዉና የቀደመዉ ትዉልድ የመሪነት በትሩን ለአዲሱ ትዉልድ ማሰረከብ አለበት አዲሱም ትዉልድ ያለትላንት ዛሬ የለምና ያለፈዉን ትዉልድ ከማማረር ይልቅ አመስግኖ ማክበር ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከቀድሞዉም ትዉልድ በጎዉን በመዉሰድ ከትዉልድ ትዉልድ የሚደረገዉም ሽግግር በመተራረም ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት እኛም በቀጣይ ተተኪ መሆናችንን መርሳት የለብንም ብልዋል፡፡
ከመምህሩ የሚበልጥ ደቀመዝሙር ያላፈራ መምህር መምህር እንደማይባል ሁሉ ተተኪ መሪ ያላፈራ ትዉልድም መሪ አይባልም የተሻለ መሪም ማፍራት ይጠበቅብናል ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀይማኖት አባቶች ፤አስተማሪዎች ወላጆች ታዋቂ ሰዎች የጎሳ መሪዎች በንጹህ ህሊና በሞራል ልልና በስነምግባር በመታነጽ በቃልና በግብር ምሳሌዎች ሆነን ህዝባችንን መታደግ ይገባል ብለዋል ፡፡
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤዉ እንዲሳካ ላደረጉ ደኢህዴን እና የሀዋሳ ህዝብን አመስግነዋል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button