Ethiopia

ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ

ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ተናገሩ

አርትስ 07/ 04 /2011
የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በመቐለ መካሄድ ጀመረ ።
በጉባዔው መክፈቻ የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበርና የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂ እና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል።
ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፥ ላለፉት ሁለት አመት ተኩል በተለያዩ አቅጣጫዎች ከባድ ትግል መደረጉን እና በአሁን ሰአት ኢትዮጵያ በአስጊ እና በአጓጊ ሁኔታዎች መከበቧን ተናግረዋል።
እንደ ሀገር የሚታዩ ተግዳሮቶችን መቅረፍ እንዲቻል ሴቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ወይዘሮ ሙፈሪያት ያሳሰቡት።
ሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪያችን ለሰላም የቀረበ ነው ያሉት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ህዝብ እንደ ህዝብ ጥላቻ እንደሌለበትም ተናግረዋል።
መቼም ቢሆን ሴቶች ለሀገራዊ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ሀገሪቱ ከፊቷ የተደቀነባትን ተግዳሮቶች ማፅዳት እንደሚገባቸው ለጉባኤው ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ በተለያየ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሴቶች ተሳታፊ ናቸው።
በዚህ ጉባዔ ድርጅቱ ለሴቶች የተሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ የሚያስቀጥል አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የተደራጀ የሴቶች ተሳትፎ ለሀገራዊ ለውጡ የጎላ ፋይዳ እንዳለው በማሰብ ኢህአዴግ በሴቶች ዙሪያ እያደረገው ላለው እንቅስቃሴ ጉባኤው ተጨማሪ ጉልበት ይኖረዋል ተብሏል።

ኤፍ.ቢ.ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button