SportSports

የዬሮ 2020 የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች ተጀምረዋል

ትናንት ምሽት በርካታ የምድብ መክፈቻ የማጣሪያ ግጥሚያዎች ተደርገዋል፡፡

በምድብ ሶስት ቤላሩስን ያስተናገደችው ኔዘርላንድስ 4 ለ 0 ድል አድርጋለች፡፡ ሜምፊስ ዲፓይ በጨዋታ እና በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ጆርጂዮ ዊናልደም እና ተከላካዩ ቨርጂል ቫን ዳይክ ቀሪዎቹን ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

እዚሁ ምድብ ሰሜን አየርላንድ በኒያል ማክጊን እና ስቴቨን ዳቪስ ጎሎች ኢስቶኒያን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

በአምስተኛው ምድብ ክሮሺያ ዛግሬብ ላይ አዘርባጅንን 2 ለ 1 ድል ስታደርግ ፤ ስሎቫኪያ ሀንጋሪን 2 ለ 0 ረትታለች፡፡

ምድብ ሰባት ላይ ፖላንድ ወደ ኦስትሪያ ተጉዛ በክርዚስቶፍ ፒያቴክ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡ ሰሜን ሜቄዶኒያ ላቲቪያን 3 ለ 1 ስትረታ፤ እስራኤል ከ ስሎቬኒያ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይታለች፡፡

በዘጠነኛው ምድብ ቤልጂየም ሩሲያን 3 ለ 1 ድል ስታደርግ፤ የዩሪ ቴሊማንስ እና ኤዲን ሀዛርድ ሁለት ግቦች ቡድኑ አሸናፊ ሁኖ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡

እዚሁ ምድብ አስገራሚው ውጤት ስኮትላንድ ወደ ካዛኪስታን አምርታ የ3 ለ 0 ሽንፈት ገጥሟታል፡፡ ቆጵሮስ ሜዳዋ ላይ ሳን ማሪኖን የምሽቱን ሰፊ የግብ መጠን አስመዝግባ 5 ለ 0 ድል አድርጋለች፡፡

የሌሎች ምድቦች የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያዎች ዛሬ የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button