AfricaSportSports

ግብፅ የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ ተነገረ

ግብፅ የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ እንደምታዘጋጅ ተነገረ

የአፍሪካ እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ካፍ) ካሜሮንን የ2019 የቶታል ካፍ የአፍካሪካ ዋንጫ ቅድመ ዝግጅትሽ አመርቂ አይደለም በማለት በህዳር ወር እንደነጠቃት ይታወሳል፡፡

ከዚያም ካፍ ከስድስት ወራት በኋላ የሚካሄደውን ዝግጅት በፍቃደኝነት የሚያሰናዳ አካል ካለ ብሎ ባወጣው ማስታወቂያ ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ ማመልከቻቸውን ማስገባታቸው ይታወቃል፡፡

የካፍ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አዘጋጁን ሀገር በመጪው ዕሮቡ አስታውቃለሁ ቢልም፤ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ግብፅ የተሻለ አቅም አላትና እሷ ታስተናግድ በማለት ፍቃድ ስጥቷታል፡፡ ይህን ተከትሎ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር የአፍሪካ ዋንጫን ለአምስተኛ ጊዜ የምታሰናዳ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ካፍ የግብፅን የአዘጋጅነት ውሳኔ በሴኔጋል መዲና ዳካር በሚደረግ የ2018 የኮከቦች የሽልማት ስነ ስርዓት በይፋ ያበስራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ውድድሩ ከስድስት ወራት በኋላ ሰኔ ወር ላይ በ24 ብሄራዊ ቡድኖች መካከል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የ2019ኛውን ውድድር የተነጠቀችው ካሜሮን ወደ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅነት የተቀየረች ሲሆን የ2021 አዘጋጅ አይቮሪ ኮስት ደግሞ ወደ 2023 ተሸጋግራለች፡፡ ምዕራብ አፍሪዊቷ አይቮሪ ኮስት ግን ለስፖርት ገላጋዮች ፍርድ ቤት አቤት እላለሁ እያለች ነው፡፡

የ2023 ውድድርን እንድታዘጋጅ እድል የተሰጣት ጊኒ በእግር ኳስ ፌዴሬሽኗ በኩል ትናንት እንዳስታወቀችው የአዘጋጅነቷን ጊዜ ወደ 2025 መግፋት እንደምትችል ነው፡፡

ቢቢሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button