COVID-19HealthNews

በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2012 በኒው ዚላንድ ከ24 ቀናት በኋላ ሁለት የኮሮሮናቫይረስ ታማሚዎች መገኘታቸው ተሰማ:: ቢቢሲ በዘገባው እንዳስነበበው ኒው ዚላንድ የኮሮናቫይረስን አጥፍቻለሁ ካለች በኋላ ነው ከእንግሊዝ በመጡ ሁለት ሰዎች ቫይረሱ የተገኘው፡፡ ኒው ዚላንድ ባለፈው ሳምንት አዲስ የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች አለመገኘታቸውን ተከትሎ በሀገር ውስጥ ጥላቸው የነበሩትን የዕንቅስቃሴ እገዳዎች ሙሉ በሙሉ አንስታለች፡፡ አሁን ላይ ከእንግሊዝ በልዩ ፈቃድ ወደ ሀገሯ የገቡት ሁለት የቤተሰብ አባላት ቫይረሱ እንዳለባቸው መረጋገጡ በተንሹም ቢሆን ስጋትን ፈጥሮባታል ነው የተባለው፡፡ በሀገር ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች እንዲነሱ ብትወስንም የውጭ ሀገር ጉዞዎች ግን በልዩ ፈቃድ ካልሆነ አሁንም ገና እገዳው አልተነሳላቸውም፡፡ ተፈቅዶላቸው ወደ ሀገር የሚገቡ ተጓዦችም ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ተመርምረው ጤነኛ መሆናቸው ከተረጋገጠ ነው ወደሚፈልጉት ቦታ የሚሄዱት ተብሏል፡፡ የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀሲንዳ አርደን የንግድ ተቋማት እነዲከፈቱ እና ዜጎቻቸው እንደልብ እንዲንቀሳቀሱ ሲፈቅዱ ወደፊት ችግሩ ተመልሶ አይገጥመንብ ብለን አንዘናጋም የሚል መልእክት አስተላልፈው ነበር፡፡ ኒው ዚላንድ 1 ሺህ 506 ዜጎቿ በኮሮናቫይረስ ተይዘውባት የነበረ ሲሆን ከነዚህ መካከልም 22 ሰዎች
መሞታቸው የሚታወስ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button