Health

እጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ08፣ 2012 ከእጅ ንክኪ ነፃና ለአጠቃቀም ቀላል የእጅ ማስታጠቢያ የፈጠራ ውድድር ምዝገባ ተጀመረ::ውድድር በዩ. ኤስ. ኤድ ትራንስፎርም ዋሽ እና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ትብብር ነዉ የተዘጋጀዉ፡፡

የውድድሩ አዘጋጆች በሰጡት መግለጫ ማንኛውም በቴክኒክና ሞያ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችም ይሁኑ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ የሚሰሩ ግለሰቦች መወዳደር ይችላሉ፡፡በሚኒስቴሩ የጤና አጠባበቅ ምክትል ዳይሬክተር አቶ አሽረፈዲን ዮያ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ዉድድሩ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በተጨማሪም አሁን ያለው የእጅ ማስታጠቢያ አገልግሎት ብዙ ጉድለቶች እንዳሉበትና መፍትሄ እንደሚሻም ገልጸዋል፡፡

በ ፒ.ኤስ. አይ የዩ. ኤስ. ኤድ ትራንስፎርም ዋሽ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሞንቴ አቼንባች ገበያ መር በሆነ መንገድ የንፅህና መገልገያዎችን በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ለማቅረብ እይተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡የዋን ዋሽ ሀገራቀፍ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ አብይ ግርማ የንፁህ ውሃ መጠጥ አገልግሎትን ለማዳረስና የንፅህና አገልግሎት አሰጣጥን ተፈፃሚ ለማድረግ አላማን ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልፀው ቀጣይነት እንዲኖረውም መሰራት አለበት ሲሉ አመላክተዋል፡፡በዉድድሩ ተሰትፈዉ ለሚያሸንፉ የፈጠራ ባለሞያዎችም ፤ወደስራ እንዲገቡ ይደረጋል ተብሏል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button