World News

ኢራን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ያደረጉትን የዲፕሎማሲ ስምምነት አወገዘች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 ኢራን የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችና ባህሬን ከእስራኤል ጋር ያደረጉትን የዲፕሎማሲ ስምምነት አወገዘች:: ፕሬዚዳንት ሀሰን ሩሃኒ እነዚህ ከጠላታችን እስራኤል ጋር ስምምነት የደረጉ ሁለት የአረብ ሀገራት ወደፊት እስራኤል በገልፉ አካባቢ ለምታደርስው ማነኛውም ጉዳት ተጠያቂ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

እስራኤል በፍልስጤማዊያን ወገኖቻችን ላይ በየቀኑ ወንጀል እየፈፀመች ሳለ ከሷ ጋር መተባበርና በቀጠናው የጦር ሰፈር እንድትነባ ለመፍቀድ መዘጋጀት ክህደት ነው ሲሉም ወቅሰዋል፡፡ የሩሃኒ የትችት እተያየት የተሰማው ጠቅላይ ሚኒስትር ከተባሩት አረብ ኤሜሬቶችና ከባህሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በዋይት ሀውስ ይፋዊ የዲፕሎማሲ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ሮሃኒ እስራኤል ሰሞኑን በጋዛ ሀማስ ላይ ያነጣጠረ የቦንብ ድብደባ ማድረጓን አስታውሰው ከእሷ ጋር መስማማት ማለት ለዚህ ጥቃት ተባባሪ መሆን ማለት ነው ብለዋል፡፡ የዚህ ስምምነት ዋነኛ አደራዳሪ የሆኑት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ የኢራን ቀንደኛ ጠላት ሳዑዲ አረቢያን ጨምሮ ይህን ስምምነት በርካታ የአረብ ሀገራት በቅርቡ ይቀላቀላሉ የሚል ተስፋ አለኝ እያሉ ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button