Ethiopia

ህበረት ለበጎ ከቄራና ጎፋ ወጣቶች ጋር በመተባበር ለ600 ሰዎች ድጋፍ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ4፣ 2012 ህበረት ለበጎ ከቄራና ጎፋ ወጣቶች ጋር በመተባበር ለ600 ሰዎች ድጋፍ አደረገ፡፡የማእድ መጋራት ፕሮግራሙ ብዙ ወገኖች በኮፊድ 19 ምክንያት ስራ መስራት ባለመቻላቸዉ ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች ለመድረስ የተደረገ መሆኑን የህበረት ለበጎ መስራች አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ገልጿል፡፡

ድጋፉ ከጎፋ ቄራ ወጣቶች እንዲሁም በዉጭ ሀገር ከሚገኙ ወጣቶች በተሰበሰበ 1 ሚሊዮን 35 ሺህ ብር ወጪ ደረቅ ምግቦች ድቄትና ዘይት እንዲገዛበትና እንዲለገስ ተደርጓል፡፡የከተማ አስተዳደሩም ከ11 የተለያዩ ቀበሌዎች ለተዉጣጡ በኮቪድ 19 ምክንያት ችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች ወጣቶቹ በመተባበር ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button