EthiopiaPolitics

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ እና በአካባቢው ለብዙ ዓመታት በስደት ላይ የነበሩ 168 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት  በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በየመን ዋና ከተማ ሰንዓ እና በአካባቢው ለብዙ ዓመታት በስደት ላይ የነበሩ 168 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት  በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

በአጠቃላይ 391 ኢትዮጵያዊያን ከየመን የሚመለሱ ሲሆን ፣ በነገው ዕለትም ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ዜጎቻችን ከየመን ይመጣሉ።

ባለፈው ሳምንት በሳኡዲ አረቢያ በተለያየ ምክንያት ታስረው የነበሩ 368 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ገልጽዋል፡፡

መንግስት ስደተኞቹ ካሉባቸው አገራት መንግስታት እና ከዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ጋር በመተባበር ዜጎች በሰላም ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ባደረገው ስምምነት መሰረት በቀጣይም በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ያጋጠማቸውን ዜጎች ወደ አገራቸው የመመለሱን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጽዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button