Ethiopia

ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 24፣2013 ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ ትምህርት ቤቶች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ:: የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተገቢ ያልሆነ የክፍያ ጭማሪ በሚፈጽሙ የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ አለ ፡በከተማዋ አስተዳደር የሚገኙ የግል ትምህርት ተቋማት በትምህርቱ መስክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እና ለከተማው ነዋሪ የስራ እድል ከመፍጠር እረገድ ሚናቸዉ ላቅ ያለ ነው ብሏል ቢሮው ባወጣው
መግለጫ፡፡

እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በተከሰተበት ወቅት የተቀመጠውን ፕሮቶኮል በማክበር የመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲከናወን እና ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ላደረጉት ስራ እውቅናም እንሰጣለን ነው ያለው፡፡ ይሁን እንጂ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለትምህርት አገልግሎት እና ምዝገባ በተቀመጠላቸው
የማስፈጸሚያ ማኑዋል መስረት መስራት ሲገባቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች የተጋነነ ዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ብሏል፡፡

ለቢሮው እና ለወላጅ ምላሽ በመስጠታቸው እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰዳቸው በ41 ትምህርት ተቋማት ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ እንዲነሳላቸው እና አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉንም ቢሮው አመልክቷል፡፡ ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና የአብሮነት እሴቶችን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን
ማዕከል በማድረግ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።

አሁን ባለንበት ወቅት ተደጋግፈን የምናልፍበት እንጂ አንዱ በሌላው ላይ ጫና የሚፈጥርበት እንዳልሆነ ታውቆ የግል ትምህርት ቤቶች ከደንበኞቻቸው ጋር በመነጋገር እንዲሰሩ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button