EthiopiaSocial

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ በዛሬዉ ዕለት በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸዉ የነበሩ ውግዘቶችን እንደሚያነሳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ በዛሬዉ ዕለት በውጭ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸዉ የነበሩ ውግዘቶችን እንደሚያነሳ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ሀገር ውስጥ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ በ1984፣ 1985 እና በ1999 ዓመተ ምህረቶች አሜሪካ በሚገኘው ሲኖዶስ ላይ አሳልፏቸው የነበሩ ውግዘቶችን በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልዐተ ጉባዔ ዛሬ እንደሚያነሳ ተናግሯል።
በመግለጫው፥ በመጪው ረቡዕ ወደ ሀገር ቤት የሚመለሱትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በደማቅ ስነ ስርዓት አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገም ነዉ ብሏል።
በዚህም ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ መንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ድረስ የቤተ ክርስቲያኗን ቀኖና በጠበቀ መልኩ የአቀባበል ስነ ስርዓቱ እንደሚከናወን ታውቋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button