Featured

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንዲያገኙ እየሰራሁ ነው አለ:: በሊባኖስ በደረሰዉ ፍንዳታ የ1 ኢትዮጵያዊ ህይወት ማለፉንና 9 ኢትዮጵያዊያን ደግሞ ቀላልና ከባድ አደጋ እንደደረሰባቸዉ የሚኒስሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲን ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡ በቤይሩት በሚገኙት መጠለያዎች ዉስጥ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ግን ጉዳት እንዳልደረሰባቸዉና በጥሩ ደህንነት እንደሚገኙ ነዉ የተነገረ ሲሆን ወደ ፌት ግን ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ተታለዉ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵዊያንም ባሉበት አካባቢ እንዲረዱ ለማድረግ ከኢትዮጵያን ዲያስፖራ ማህበረሰብ ጋርና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ዉይይት ተደርጓል ብለዋለወ ቃል አቀባዩ፡፡ ከዚህ ባሻገር የዜጋ ተኮር ዲፖሎማሲን በተመለከተም ከመካከለኛዉ ምስራቅ ሀገራት ማለትም ከሱዳን ከካርቱምና ከሳዉዲ እንዲሁም ከዶሃ እስር ቤቶች 218 ሰዎች መመለሳቸዉ ተገልጿል ወደ ሀገራቸዉ ከተመለሱም በኋላ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጥረት ላይ መሆናቸዉን የዉጪ አምባሳደር ዲና ገልፀዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button