Africa

የሶስት ቀናት የትራፊክ አደጋ ደቡብ አፍሪካን በርካታ ዜጎች አሳጥቷታል

የሶስት ቀናት የትራፊክ አደጋ ደቡብ አፍሪካን በርካታ ዜጎች አሳጥቷታል

አርትስ 10/04 /2011

በሀገሪቱ ካፈው ቅዳሜ እስከ ሰኞ ባሉት ሶስት ቀናት ብቻ  94 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው አደጋው የደረሰው በጆሀንስገርግ፣ በፕቶሪያ፣ በኬፕታወን እና በጋውቴንግ አውራጃዎች ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ የክብረ በዓል ወቅት በመሆኑ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ ተለያ ቦታዎች በዓሉን ለማክበር  ከከተማ ውጭ መኪና ያሽከረክራሉ ፡፡

የጆሀንስበርግ ከተማ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዋይኔ ሚናር በተለይ ለአደጋው መባባስ ዋናው ምክንያት  ከተገቢው ፍጥነት በላይ ማሽከርከር  መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቃል አቀባዩ እንዳሉት ፌስቲቫሉን ለመካፈል ከከተማ ውጭ ከተጓዙት መካከል 20 ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች በሰዓት 206 ኪሎ ሜትር በሆነ ፍጥነት ሲነዱ በመገኘታቸው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሚናር አያይዘውም የታህሳስ ወር ከገባ ጀምሮ የትራፊክ ደንብን ተላልፈው የተገኙ  2ሺህ 99 አሽከርካሪወች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ባለፈው ዓመት ብቻ 14 ሺህ 50 ሰወች በትራፊክ አደጋ መሞታቸውን   የሀገሪቱ መንግስት ባወጣው  በሪፖርቱ ይፋ አድጓርል፡፡

በሀገሪቱ በየጊዜው ከሚከሰተው የትራፊክ አደጋ መካከል 85 በመቶ የሚሆነው በአሽከርካሪዎች ስህተት የሚደርስ ነው ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button