NewsWeather

በመጪው ዓርብ አመታዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መረሃ ግብር በይፋ ይጀመራል::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 በመጪው ዓርብ አመታዊ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተካላ መረሃ ግብር በይፋ ይጀመራል::
ዓርብ ግንቦት 28/ 2012 ዓመታዊውን የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ  መረሃ ግብር በይፋ እንደሚጀመር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ ፡፡
ባለፈው ዓመት እያንዳንዳችን ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለን ያቀድነውን አሳክተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ በሀገራችን ከተጋረጠው ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር እየተፋለምን ቢሆን ዕቅዳችንን እናሳካለን ሲሉ በመሃበራዊ ትስስሰር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡አንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ በዚህ አመት 5 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዕቅዳችንን እናሳካዋለን  በማለት እያንዳንዱ ቤተሰብ አካላዊ ርቀትን ጠብቆ  ዐሻራውን የማሳረፍበት መንገድ እንደሚመቻችም ነው የገለፁት::

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button