EthiopiaSport

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ እንደሚካሄድ ተገለፀ::

የምድብ ሀ አሸናፊ ባህርዳር ከነማ(የጣናው ሞገድ) ከምድብ ለ አሸናፊ ደቡብ ፖሊስ የሚያደርጉት የፍፃሜ የዋንጫ ጨዋታ አዳማ ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል፡፡ ይሄ ጨዋታ ቀድሞ በወጣው መርሃ ግብር ድሬዳዋ ላይ ይደረጋል የተባለ ቢሆንም የድሬዳዋ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት መታረሱ የቀንና የቦታ ለውጥ ለመደረጉ ዋነኛው ምክንያት ሆኗል፡፡ በዚህም መሰረት የባህርዳር ከነማና የደቡብ ፖሊስ የዋንጫ ጨዋታ የፊታችን ማክሰኞ ነሀሴ 29 አዳማ ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የምድብ ሀ እና ለ ሁለተኛ ደረጃ በመሆን ያጠናቀቁት ሽረ እንደስላሴና ጅማ አባቡና ጨዋታ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት ሀዋሳ ላይ ይካሄዳል ተብሏል፡፡ የዚህ ጨዋታ አሸናፊ 3ኛው ወደ የ2011ዓ/ም የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ውድድር አዳጊ ቡድን ይሆናል::
ባህር ዳር ከነማ እና ደቡብ ፖሊስ አስቀድመው ማለፋቸው ይታወሳል::

አርትስ 23/12/10

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button