Africa

የአውሮፓ ህብረት በጋዛ ሰርጥ ያለው ውጥረት ያሳስበኛል አለ፡፡

የአውሮፓ ህብረት በጋዛ ሰርጥ ያለው ውጥረት ያሳስበኛል አለ፡፡

የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሀላፊ ፍሬዴሪካ ሞጎሮኒ እንዳሉት በአካባቢው የሚደረጉ የሮኬት ተኩስ ልውውጦችና እስራኤል የምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡

አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከ2014 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣው የአካባቢው ውጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል ሞጎሮኒ፡፡

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ካውንስል ባደረገው ስብሰባ ጉዳዩን በአጀንዳነት ቀድሞ ባይዘውም ነገሩ ስላሳሰበው ተወየያቶበታል ብለዋል ሀላፊዋ፡፡

በውይይቱ ወቅትም ሁላችንም የተስማማነው ሁለቱም ወገኖች በፍጥነት ጥቃት አቁመው ወደሰላም መንገድ እንዲመጡና የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ መልዕክት ማስተላለፍ አለብን በሚለው ሀሳብ ላይ ነው ብለዋል ሞጎሮኒ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button