Africa

የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 የአልጄሪያው ፕሬዚዳንት አብደልመጅድ ቲቦኒ የሀገሪቱን ፓርላማ በትነው አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ይህን ውሳኔያቸውን ያሳወቁት አልጄሪያ የሰማእታት ቀንን በምታከብርበት ወቅት ነው ተብሏል፡፡ ቲቦኒ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት የተለያዩ የፓርቲ መሪዎች ጋር ተደጋጋሚ ስብሰባዎችና ምክክሮችን ካደረጉ በኋላ መሆኑ ነው የተሰማው፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፕሬዚዳንቱና የካቢኔ አባሎቻቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ከህዝቡ ግፊት በርክቶባቸዋል፡፡በርካታ አልጄሪያዊያን ፕሬዚዳንት ቲቦኒና በሀገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን በእጁ ያስገባው የሀገሪቱ ጦር ሃይል ተወግዶ አዲስ አስተዳደር እንደመሰረት የሚል ሀሳብ ይዘው ተከታታይ ሰልፎችን ሲያካሂዱ ተስተውላል፡፡ ፓርላመውን ያፈረሱት ፕሬዚዳንት ቲቦኒ በቅርብ ጊዜ የህግ አውጭ ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ
አቅርበዋል ነው የተባለው፡፡

አልጄሪያ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠረው በ1962 ከፈረንሳይ ቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች ጀምሮ በስልጣን ላይ ያለው ገዥው ፓርቲ አሁን ላይ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነቱን ያጣ ሲሆን ተደጋጋሚ ተቃውሞ እየደረሰበት ይገኛል፡፡ የፕሬዚዳንቱ ውሳኔም ይህን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማርገብ ያለመ ሳይሆን እንደማይቀር አስተያየት ሰጭዎች ያናገራሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button