Uncategorized

የኬንያ ፖሊሶችስ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ተኩሰው ሶስት ሰዎች መግደላቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012  የኬንያ ፖሊሶችስ ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ተኩሰው ሶስት ሰዎች መግደላቸው ተሰማ:: ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት የታክሲ ሾፌሮች እና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ሲሆኑ ምክንያታቸውም የሥራ ባልደረባቸው የሆነ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ህግን ተላልፏል ተብሎ በመታሰሩ ነው ተብሏል፡፡ የኬንያ ፖሊስ ኢስፔክተር ጄኔራል ሂላሪ ሙቲያማቢያ በሰልፎቹ ላይ ተኩሰው የሰው ህይዎት እንዲያልፈ ምክንያት ናቸው የተባሎ የፖሊስ አባላት እንዲታሰሩ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡ በፖሊሶቹ እርምጃ የተበሳጩት ሰልፈኞቹ የአንድ የፖሊስ መኮንን ቤት ማቃጠላቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ በፖሊሶችና በተቃዋሚዎቹ መካከል ግጭቱ የተፈጠረው ሌሶስ በተባለችው የኬንያ ከተማ ሲሆን ፖሊስ ጥይት ለመተኮስ ያስገደደው ተቃዋሚዎቹ በህግ አስከባሪዎች ላይ ጥቃት በመሰንዘራቸው መሆኑን ተናግሯል፡፡የኬንያ ፖሊስ በዜጎች ላይ ከልክ በላይ የሆነ ሃይል ይጠቀማል የሚል ተደጋጋሚ ወቀሳ የሚደርስበት ሲሆን ከአሁን ቀደምም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ከእንቅስቃሴ እገዳ ጋር በተያያዘ መገደላቸው ተነግሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button