EthiopiaSocial

እንግሊዝ  ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ቅርሶች ውስጥ  11 ፅላቶች  በእንግሊዝ መኖራቸው  ተገለፀ

እንግሊዝ  ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው ቅርሶች ውስጥ  11 ፅላቶች  በእንግሊዝ መኖራቸው  ተገለፀ

በመቅደላ ጦርነት ወቅት እንግሊዝ ከኢትዮጵያ ከወሰደቻቸው  ቅርሶች ውስጥ  በቅርቡ ወደሀገሩ የተመለሰው የንጉስ አፄ ቴዎድሮስ ሹሩባን ጨምሮ  11 ፅላቶቸ መኖራቸውን  የበህል እና  ቱሪዝም ሚንስቴር  ሚንስትር  ዶክተር ሂሩት ካሳው ተናግረዋል፡፡

በታሪክ አጋጣሚ ከሀገር ተወሰደው ከቀሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መሀከል  ከ 349  በላይ የብራና መፅሃፍት  መኖራቸውንም የጠቀሱት ሚኒስትሯ   እነዚህ ቅርሶች ለሀገራችን  ህዝብ የሚሰጡት ፋይዳ በምንም የማይታካ በመሆኑ ከእንግሊዝ ሀገር  ጋር በተደረገ ደርድር በቅረቡ  ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡

እንግሊዞች  ለ151 ዓመት ያህል ጠብቀው ያቆዩትን  ቅርሶች  አሁን ያለው ትውልድ   ተረክቦ ቅርሶቹን በሚገባ የመንከባከብ  ሃላፊነት እንዳለበት   የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ  ዶክተር ሂሩት  ካሳው ተናግረዋል፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button