EthiopiaSocial

ቢዘገይም በፓርኩ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የሚችል  ሄሊኮፕተር ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

ቢዘገይም በፓርኩ ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የሚችል  ሄሊኮፕተር ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ላይ የተነሳውን እሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር ከኬንያ ለማስመጣት በሂደት ላይ መሆኑን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል፡፡  

ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ጉዳዩን ለማስፈፀም እየተሰራ መሆኑን በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የውጭና ዓለማቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ለአርትስ ተናግረዋል፡፡

ኬንያ ፈቃደኛ መሆኗንና ጉዳዩን በቶሎ ለማሳካት ኢትዮጵያ ከኬንያ ጋር እየተነጋገረች መሆኑንም አቶ ገዛኸኝ ተናግረዋል።

በዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሩ አቶ ጌትነት ይግዛው ለአርትስ ቲቪ በስልክ በሰጡን መረጃ መሰረት፣ከዚህ ቀደም የእሳት ቃጠሎ በዚሁ ፓርክ ተነስቶ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አርሶአደሮች፣ የወጣት አደረጃጀቶት እና ሌሎችም ተረባርበው አጥፍተውት ነበር፡፡

ነገር ግን አሁንም ለመቆጣጠር አስቸጋሪ በሆነ መልኩ ቃጠሎው  ዳግም ተነስቷል፡፡ ሁሉም አካል ለፓርኩ ቃጠሎ መጥፋት እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡  

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button