EconomyEthiopiaPoliticsSocial

በቤት ልማት እና ሌሎችም መስኮች ባለሀብቱን ለማሳተፍ የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው አሉ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ

በትናንቱ ምሽትም ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ቃል ተገብቷል

ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከባለሀብቶች እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ባደረጉት ውይይትና ቆይታ ባለሀብቱ በመጪው አዲስ አመት በተለያዩ የበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ እንዲሳተፍ ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ የትምህርት ቁሳቁሶች እና ከ35 ሚሊየን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ቃል ተገብቶአል ።
ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን አርአያ በመከተል ሁሉም ሰው ከጎረቤቱ ምልከታውን እንዲጀምር አሳስበዋል ።
ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከባለሀብቶች እና ከንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት
አሁን በሀገራችንም ሆነ በመዲናችን እየታየ ያለውን በመዋቅር የተተበተበ ሌብነትና ሙስና በማስወገድ ፍትሃዊነትንና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ስርዓት ለመዘርጋት በከፍተኛ ትጋት እየተንቀሳቀስን ነው። ማለታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት ያስታወቀ ሲሆን መንግስት ከአሁን ወዲህ በሁሉም ነገር እጁን አስገብቶ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ እንደማይዘልቀው የተገነዘበበት ወቅት ነው ማለታቸውን ጨምሮ አስታውቋል ፡፡
በዋናነት መንግስት እጁን ለማስወጣት በወሰነበት የቤት ልማት እንዲሁም በበርካታ መስኮች ባለሀብቱን ለማሳተፍ የፐብሊክ ፕራይቬት ፓርትነርሺፕ/ppp/ ለመፍጠር የህግ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።

አርትስ 25/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button