EconomyEthiopiaPoliticsSocial

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ

አርትስ 04/03/2011

 

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ መሰረት ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ69 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 17 ብር ከ78 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ በሊትር 17 ብር 78 ሳንቲም፤

ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 15 ብር ከ41 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 14 ብር ከ90 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅበሊትር 27 ብር ከ08 ሳንቲም ሆኗል።

እንደ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገለፃ አለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት ነው  በነዳጅ ምርቶችየችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ የተደረገው፡፡

የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከዛሬ ህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎችእንደሚተገበር ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button