AfricaEthiopiaSportSports

ዋልያዎቹ በወዳጅነት ጨዋታ ከቡሩንዲ አቻቸው ጋር ተጫውተው በአቻ ውጤት ተለያዩ፡፡

አርትስ ስፖርት 27/12/2010
ለረዥም ጊዜ ከውድድር ርቆ የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአዲስ አሰልጣኝ እየተመራ የመጀመሪያ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ከቡሩንዲ አቻው ጋር ዛሬ በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም አካሂዷል፡፡
በምዕራብ አፍሪካዋ ሀገር ካሜሩን አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ ለመካፈል ሁለተኛ የምድብ ማጣሪያ ግጥሚያውን ለማድረግ ከጋና፤ ሴራሊዮን እና ኬኒያ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን ጳጉሜ 4 ከሴራሊዮን ብሄራዊ ቡድን ጋር ሀዋሳ ላይ ይገጥማል።
ከሶስት ሳምንት በላይ በሀዋሳ ዝግጅት እያደረገ ብሔራዊ ቡድኑ ለሴራሊዮኑ የማጣሪያ ጨዋታ ያግዘው ዘንድ ከቀኑ በ10:00 ከብሩንዲ ብሔራዊ ቡድን ጋር ተጫውቶ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይቷል።
በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የሚመራው ቡድኑ በቅድሚያ ግብ ያስተናገደ ሲሆን በሁለተኛው አጋማሽ በ58ኛው ደቂቃ ሻባኒ ሁሴን ብሩንዲን ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም በቅርቡ በተጫዋቾች ዝውውር ከደደቢት ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያመራው ጌታነህ ከበደ (ሰበሮ) በ72 ደቂቃ ቡድኑን አቻ አድርጓል፡፡
አሰልጣኝ አብርሀምም የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡
በጨዋታው በኢትዮጵያ ቡድን በኩል ሳምሶን አሰፋ፤ ሳላሀዲን በርጊቾ፤ አስቻለሁ ታመነ፤አህመድ ረሺድ፤ ሙሉዓለም መስፍን፤ አብዱልከሪም መሐመድ፤ ታፈሰ ሰለሞን፤ አማኑኤል ዮሀንስ፤ ዳዋ ሆቴሳ፤ አዲሰ ግደይ እና ጌታነህ ከበደ በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ተካተው ነበር፡፡ ሙጂብ ቃሲም፤ አዲስ ግደይ፤ ተክለማርያም ሻንቆ፤ ሰለሞን ሀብቴ፤ ናትናኤል ዘለቀ እና ሄኖክ አዱኛ ተቀይረው ገብተዋል፡፡
አምሳሉ ጥላሁን፣ እስራኤል እሸቱ፣ ተመስገን ካስትሮ፣ በዛብህ መለዮ፣ ዐወት ገ/ሚካኤል፣ በኃይሉ አሰፋ እና አቤል ማሞ በጉዳት ከወዳጅነት መርሀግብሩ ውጭ ሲሀኑ በውጪ ሀገር እየተጫወቱ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል የፔትሮጄቱ ሽመልስ በቀለ ቡድኑን ተቀላቅሏል፤ ጨዋታውንም በስቴድየም ተገኝቶ ተመልክቷል።
24 የልዑካን ቡድን አባላትን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ብሔራዊ ቡድኑ ግማሽ ወጪው በኢትዮጵያ እግር ኳር ፌድሬሽን እንደተሸፈነለት እየተነገረ ይገኛል።
ጨዋታውን ኢትዮጵያውያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ሲመሩት በዋና ዳኝነት ብሩክ የማነ ብርሀን መርተውታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button