EthiopiaPoliticsSocial

አዲሰ አባበ ውስጥ እያካሄደ ባለው የማጣራት ሥራ ባለቤት የሌላቸውን ሕንፃዎችና ታጥረው የተቀመጡ መሬቶችን ማግኘቱን የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

 

ሃላፊነት በተረከብን በማግስቱ 10 ቡድኖችን አደራጅተን በሁሉም ክ/ከተሞች ያሰማራን ሲሆን በአንድ ወር ውስጥ በመጣው መረጃ ብዙ የተሰሩ ህንፃዎች ባለቤት የላቸውም፤ የታጠሩ ቦታዎች ባለቤት የላቸውም፤ ብዙ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በግለሰብ ተይዘው አሉ፤ ይሄንን አጥርተን ለህዝብ በዝርዝር ይፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ምክትል ከንቲባው አቶ ታከለ ኡማ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቃለ-ምልልስ ባደረጉበት ወቅት ሲናገሩ እስከ ፊታችን አዲስ ዓመት ድረስ የማጣራት ሥራው ተጠናቅቆ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ አመልክተዋል።
ብዙ ሃብት እያላቸውም የቀበሌ ቤት እና ኮንዶሚኒየም ይዘው የድሃውን ሃብት የሚሻሙ ብዙ ናቸው ያሉ ሲሆን ይሄንን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲፋረዳቸው እናደርጋለን በማለት ተናግረዋል፡፡ ለጊዜው እንዲቆም የተደረገው የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችም መስከረም ላይ ይጀምራል ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button