Africa

ትሪፖሊ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር ወድቃለች፡፡ 

ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እውቅና የተሰጠው የሊቢያ መንግስት በትሪፖሊና አካባቢዋ የተቀሰቀሰው ግጭት እስኪረጋጋ የእቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ አስፈላጊ ነው ብሏል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው በሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች የተቀሰቀሰው ግጭት 39 ሰዎች ህይወታቸውን አንዲያጡ እንዲሁም ከ100 ያላነሱት ደግሞ ቁስለኞች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በተፋላሚዎቹ መካከል የተፈረመው የተኩስ አቁም ስምምነት በቀናት ውስጥ ተጥሶ ወደ ግጭት ማምራታቸውን አውግዘዋል፡፡
እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያንና አሜሪካ በበኩላቸው ሁለቱም ወገኖች በሊቢያ የተጀመረውን የፖለቲካ ሂደት የሚያደበዝዝ ተግባር ከመፈጸም አንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
ሊቢያ በቅርቡ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች መሆኑ ይታወቃል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button