AfricaEthiopiaPoliticsSocial

ከ20 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያው የኢትዮ-ሶማሊያ የኤክስፐርቶች ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

አርትስ/29/12/2010
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት በድረ ገጹ እንዳስነበበው በሁለቱ ሀገራት መሀከል ያለው ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረ ወዳጅነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በተካሄደው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ በሁለትዮሽ፣ በጋራ ትብብር፣ በኢኮኖሚ እና በቀጠናው ሰላም ዙሪያ ተወያይተዋል።
በስብሰባዉ ላይ የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ ባደረጉት ንግግር የኤክስፐርቶቹ ስብሰባ በቀጣይ ለሚካሄድ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ሁኔታዎችን የማመቻቸት ኃላፊነት እንዳለበት ተናግረዋል፤ ከረጅም ዓመታት በኋላ የተካሄደው ይህ ስብሰባ ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
የጋራ ኮሚቴው መመስረት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ መልካም ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚረዳና የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስከበር ከፍተኛ ሚና እንዳለውም ተገልጿል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button