Sport

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ታላላቆቹ ክለቦች ተሸንፈዋል

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ታላላቆቹ ክለቦች ተሸንፈዋል

አርትስ ስፖርት 04/04/2011

በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ከምድብ አምስት እስከ ስምንት በሚገኙ ቡድኖች መካከል ትናንት ምሽት ተካሂዷል፡፡

ምድብ አምስት ላይ አያክስ ከባየር ሙኒክ 3 ለ 3 ሲለያዩ፤ ግቦቹን ለባየር ሙኒክ ሉዋንዶውስኪ (2)፣ ኮማን እና ዱሳን ታዲች (2) እና ታግሊያፊኮ አስቆጥረዋል፡፡ ቤኔፊካ ኤ.ኢ.ኬ አቴንስን 1 ለ 0 በመርታት በ7 ነጥብ ወደ ኢሮፓ ሊጉ ተሻግሯል፤ ሙኒክ በ14፣ አያክስ በ12 አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቀዋል፡፡

በምድብ ስድስት  ማንችስተር ሲቲ ሆፈንየምን አስተናግዶ በሊሮይ ሳኔ ግቦች 2 ለ 1 ድል ሲያደርግ፤ ከምድቡ ሻክታር ዶኔስክ ከ ሊዮን 1 ለ 1 ተለያይተዋል፡፡ ሲቲ ምድቡን በ13 ነጥብ ቀዳሚ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፤ ሊዮን በ8 ተከትሏል፤ ሻክታር ወደ ኢሮፓ ሊጉ ተቀላቅሏል፡፡

በሰባተኛው ምድብ ደግሞ ሪያል ማድሪድ በሜዳው በሲ.ኤስ.ኬ.ኤ ሞስኮ የ3 ለ 0 ሽንፈት ሲያስተናግድ፣ ሮማ በሊዮን 2 ለ 1 ተረትቷል፡፡ ይሁን እንጅ ከምድቡ ማድሪድ ቀዳሚ ሲሆን ሮማ ሁለተኛ ሆነው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል፡፡ ቪክቶሪያ ፕለዘን የኢሮፓ ሊግ ተሳታፊነቱን አግኝቷል፡፡

በመጨረሻው ምድብ ከምድቡ አስቀድመው ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉት ዩቬንቱስና ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፤ ቫሌንሲያ ዩናይትድን፣ ያንግ ቦይስ ደግሞ ዩቬንቱስን በተመሳሳይ 2 ለ 1 ረትተዋል፡፡ ቫሌንሲያ አስቀድሞ የኢሮፓ ሊግ ተሳትፎውን አረጋግጧል፡፡

ጥሎ ማለፉን የተሻገሩ ቡድኖች፡- አትቲኮ ዴ ማድሪድ፣ ቦርሲያ ዶርሙንድ፣ ባርሴሎና፣ ቶተንሃም፤ ሊቨርፑል፣ ፒ.ኤስ.ጂ፤ ፖርቶ፣ ሻልከ 04፣ ባየርን ሙኒክ፣ አያክስ፣ ማንችስተር ሲቲ፣ ሊዮን፣ ሪያል ማድሪድ፣ ሮማ፣ ዩቬንቱስ እና ማንችስተር ዩናይትድ ናቸው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button