EthiopiaPoliticsSocial

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው ራሳቸውን እንዳጠፉ አረጋግጬባቸዋለሁ ያላቸው ነጥቦች

አርትስ 02/13/2010
ኢንጅነሩ የነበሩዋቸውን ግንኙነቶች በተመለከተ ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ምሽቱን ልጃቸውን በርትቶ ማጥናት እንዳለበት አደራ ሲሉት አምሽተዋል፡፡ በዕለቱ ጠዋት ከቤት መውጣታቸውን ከዚያም ወደ መስቀል አደባባይ ሄደው ተመልሰው ወደ ቢሮ መግባታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል ፖሊስ ፡፡ ቢሮ ከገቡ በኋላ መጸዳጃ ቤት ይመላለሱ እንደነበር እና ካሏቸው ሾፌሮች መካካል አንደኛውን ጠርተው የታሸገ ፖስታ ሰጥተውት ለማን እንደምትሰጥ እነግርሀለሁ ማለታቸውን እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ አትክልተኛውን ጠርተው ተመሳሳይ ፖስታ ወደ ኮሚዩኒኬሽን ፅ/ቤት እንዲያደርስ መላካቸውን የዚህ ተመሳሳይ መልዕክት ያለው ፖስታ ፊርማዎቹም የራሳቸው የሆኑ መኪናቸው ውስጥ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የማስታወሻው ይዘት የስራ ጫናቸውን የሚገልፅ እና ወደ ውጪ ለመውጣት ቢፈልጉም ምቹ እንዳልሆነላቸው እና የልጆቻቸውን ነገር የሚያሳስብ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡
ፀሐፊያቸውን በአስቸኳይ ቢሮ እንድትመጣ ማድረጋቸውን እንዲሁም የልጃቸውን ስልክ መስጠታቸውን እና እንድትጠይቀው አደራ ማለታቸውን ፖሊስ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡ በድጋሚ ወደ መስቀል አደባባይ መሄዳቸውን የገለፀው ፖሊስ አሟሟታቸውን እንዲሁም ከተሸከርካሪያቸው ጋር የነበረውን ሁኔታ የመኪናው መስተዋት የተሰበረው በህይወት ካሉ ለማዳን በሚል በፖሊስ አባላት እንደሆነ እንዲሁም የተገኙት ግላቮችና ሶፍቱም በተመሳሳይ ህይወታቸው መኖሩን ለማረጋገጥ የተደረገበት መሆኑን አስታውቋል፡፡
መኪናው ውስጥ የተገኘው ሽጉጥ በራሳቸው ስም የተመዘገበ ህጋዊ ፍቃድ የወጣበት ሲሆን የተኮሱት እርሳሶችም ከዚሁ ሽጉጥ የተተኮሱ መሆናቸውን በፎረንሲክ ምርመራ አረጋግጫለሁ ለዚህም ኤፍ.ቢ .አይ ድጋፍ አድርጎልናል ብሏል ፖሊስ ኮሚሽኑ፡፡
የአስከሬን ምርመራ ውጤቱ ጥይቱ በቐኝ ገብቶ በግራ የወጣ መሆኑን ማረጋገጡንም የምርመራ ቡድኑ ይፋ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ተደግፎ የተተኮሰ መሆኑን በፎረንሲክ ተረጋግጧል ብሏል፡፡
የኢንጂነሩ መኪና ሞቱ እየሰራ በሮቹ ተቆልፈው የነበረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሞይንኮ ካምፓኒ ባለሞያዎች ባረጋገጡት መሰረት መኪናው ከውጭ ሊቆለፍ አይችልም ብሏል ፖሊስ የባለሞያዎቹን ምስክርነት በመጥቀስ፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው ራሳቸውን እንዳጠፉ በነዚህና ሌሎችም ተጨማሪ ማስረጃዎች አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡
ለሞታቸው መንስኤ አንድ ምክንያት ይሆናል ያለው ከስራቸው ጋር በተገናኘ የተፈጠረባቸው ጫና መሆኑን ይህንንም በተመለከተ የምርመራ ሂደቱ ቀጣይ ይሆናል ሲል አስታውቋል፡፡ ከሚጣሩ እና ጭንቀት ውስጥ ከተዋቸው ከነበሩ ጉዳዮች መካከል የህዳሴ ግድቡ አፈፃፀም መዘግየት ብዙ ገንዘብ የወጣበት መሆኑ ከሜቴክ ጋር በተገናኘ ያለው አፈፃፀም ዝቅተኛ መሆን ሆኖ የወጣበት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑ እንዲሁም ሳሊኒ ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቁ ኢንጂነሩ ላ ከፍተኛ ጭንቀት መፍጠራቸውን አስታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button