Uncategorized

በአብዲ መሃመድ ዑመር ላይ የተጀመረው ምርመራ በ14 ቀናት ተራዘመ

በአብዲ መሃመድ ዑመር ላይ የተጀመረው ምርመራ በ14 ቀናት ተራዘመ

ፖሊስ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በቀረቡት የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር ላይ የጠየቀውን ተጨማሪ 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ችሎቱ ፈቀደ።

ችሎቱ የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት የነበሩት አብዲ ሙሃመድ ዑመርና ከሳቸው ጋር በመተባበር በተጠረጠሩት ሶስት ተከሳሾች ላይ ባለፉት14 ቀናት የተካሄደውን የምርመራ ውጤት አድምጧል፡፡

ፖሊስ ለችሎቱ እንደገለጸው በግፍ ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች ላይ የሰባት ሰዎች ምስክርነት ቃል መቀበሉን፣ በ2010 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል ድንበር በተፈጠረ ግጭት ዙሪያ ለቀረበው ክስ በመጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ ስምንት ተፈናቃዮች የምስክርነት ቃል መቀበሉን፣ እንዲሁም ከሀምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማና ሌሎች አካባቢዎች የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ የቪዲዮና የምስል መልዕክቶች የማስተረጎም ስራ ማሰራቱን አስረድቷል፡፡

ፖሊስ ወደፊት ይቀሩኛል ያላቸውን ተጨማሪ የተጎጂ ቤተሰቦችን የምስክርነት ቃል መቀበል፣ በጅምላ የተገደሉና የተቀበሩ ሰዎችን አስከሬን የማውጣት፣ ተጨማሪ ግብረ አበሮችን በቁጥጥር ስር የማዋል እንዲሁም የአስከሬን ምርመራ ውጤት መቀበል ስራዎች ለመጨረስ ተጨማሪ ቀናት እንደሚያስፈልገው ለችሎቱ በመግለጽ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት የተጨማሪ ምርመራ ጊዜ ፈቅዶለታል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button