EthiopiaSportSports

መጋቢት 1 ሊካሄዱ የነበሩ የ2ኛ ዙር የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 8 ይካሄዳሉ ተባለ

2ኛ ዙርፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች መጋቢት 8 ይጀመራሉ

 

ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club በፌስ ቡክ ገፁ ላይ ባሰፈረው መረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  የ2ኛው ዙር የፕሪምየር ሊግ  የተስተካከለ ፕሮግራም ለክለቡ መድረሱን አስታውቋል።

አስቀድሞ የወጣው መርኃ ግብር እነንደሚያሳየው የሁለተኛ ውድድር ዘመን አጋማሽ በሳምንቱ መጨረሻ እንደሚጀምር ቢያሳይም መጋቢት 1 ሊደረጉ በነበሩ ጨዋታዎች ላይ ማስተካከያ መደረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለክለባችን በላከው ደብዳቤ አስታውቋል ይላል መረጃው።

በዚህም መሠረት መጋቢት 1 ሊደረጉ የነበሩ ጨዋታዎች በሙሉ በአንድ ሳምንት ተራዝመው የሚከናወኑ ሲሆን መጋቢት 8 ሊደረጉ የተገለጹ ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ በሜዳው ሲዳማ ቡናን የሚያስተናግድበትን ጨዋታ ጨምሮ በተያዘላቸው ጊዜ እንደሚከናወኑ ተገልጿል።

የ16ኛ ሳምንት መርኃግብር

ቅዳሜ መጋቢት 7 ቀን 2011

ወልዋሎ አ.ዩ ከ ሀዋሳ ከተማ (መቐለ- ትግራይ ስታዲየም 9:00)

እሁድ መጋቢት 8 ቀን 2011

ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና (ጎንደር በአጼ ፋሲለደስ ስታዲየም9:00)

ባህር ዳር ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ (ባህር ዳር 9:00)
ወላይታ ድቻ ከ ስሑል ሽረ (ሶዶ 9:00)
ድሬዳዋ ከነማ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ድሬዳዋ 9:00)
መከላከያ ከ ደቡብ ፖሊስ (አዲስ አበባ 10:00)
ጅማ አባ ጅፋር ከ አዳማ ከተማ (ጅማ 9:00)
ደደቢት ከ መቐለ 70 እንደርታ (መቐለ – ትግራይ ስታዲየም 9:00)

በተያያዘ መጋቢት 7/2011 በኢትዮጵያ ቡና እና ስሑል ሽረ መካከል ሊከናወን የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ግንቦት 1 መሸጋገሩ ታውቋል።

ምንጭ፡- የ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ / Fasil Kenema Football Club

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button