EthiopiaPolitics

የኦነግ አመራር መስከረም አምስት አዲስ አበባ ይገባል

አርትስ 03/13/2010

በኤርትራ የሚገኘው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አመራር መስከረም አምስት 2011 ዓመተ ምህረት ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ መሆኑ ተገለፀ፡፡

በዕለቱም  1 ሺህ 300 የግንባሩ ታጣቂዎችም ከመሪያቸው ዳውድ ኢብሳ ጋር ትጥቃቸውን በመፍታት ወደ ሀገር ቤት ይገባሉ ተብሏል፡፡

ቀደም ብሎ ወደ ሀገር ቤት የገባው ልዑክ አመራር የሆኑት ኢብሳ ነገዎ እንደጠቀሱት የግንባሩ ታጣቂዎች አቀባበል በመስቀል አደባባይ ይዘጋጃል፡፡
መስከረም ሰባት ደግሞ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራንና ህበረተሰቡን ያሳተፈ የውይይት መድረክም በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እንደሚዘጋጅ አቶ ኢብሳ ጠቅሰዋል፡፡
ኤፍ.ቢ.ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button