Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አመሰገኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 21፣ 2013 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ አስተዋጽዖ ላደረጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምስጋና አቀረቡ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ አንድ ሳምንት በኋላ ዛሬ ጠዋት ከፖለቲካ ፓርቲ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቼ ኢትዮጵያ አሸናፊ ሆና የወጣችበት ሰላማዊ ምርጫ እንዲሳካ ላደረጉት አስተዋጽዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጅምር ላይ ያለውን ዴሞክራሲያችንን ለማጠናከር በምርጫ ሂደቱ ውስጥ የታዩ ተግዳሮቶች እና ክፍተቶችን በመገምገም ምን እንደተማርንባቸው ተወያይተናል ሲሉም አስታውቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button