Legal

ሳውዲ አረቢያ በዓለም ትልቅ የተባለውን የሞት ቅጣትወሰነች፡፡

ሳውዲ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱ 37 ግለሰቦች በፍርድ ቤት ጥፋኛ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም በሞት እንዲቀጡ ወስናባቸዋለች ነው ተባለው፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው በሞት የተቀጡት ግለሰቦች የሽብርተኝነት እና የአክራሪነት  ወንጀልን በማሰብ እንዲሁም ህቡዕ የሽብር ቡድን በማቋቋም ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ አድርገዋል  በሚል ነበር ክስ የተመሰረተባቸው፡፡

ሳውዲ ባለፈው ዓመት በ149 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ ያስተላለፈች ሲሆን የፈንጆቹ 2019 ከገባ ወዲህ ደግሞ 100 ሰዎች ተመሳሳይ ቅጣት ተወስኖባቸዋል፡፡

በሳውዲ ህግ መሰረት በሽብር፣ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በመሳሪያ በተቀናጀ ዘረፋ እና በሰዎች ዝውውር ወንጀል የተከሰሱ ሰዎች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ በሞት ይቀጣሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button